Measuring Time in Abushakir: From Microseconds to the Cycles of the Moon

The Abushakir tradition contains a remarkably precise system for measuring time. Days are divided through a sexagesimal, or base-60, system into progressively smaller units. The same mathematical framework can describe from a small duration (such as the duration of a heartbeat) to months and years.

A day contains ፷ ኬክሮስ, making ፩ ኬክሮስ equivalent to 24 minutes. Each unit that follows is one-sixtieth of the preceding one:

፩ ኬክሮስ = 24 minutes
፩ ካልዒት = 24 seconds
፩ ሣልሲት = 0.4 seconds
፩ ራብዒት ≈ 6.67 milliseconds
፩ ሓምሲት ≈ 111 microseconds
፩ ሳድሲት ≈ 1.85 microseconds

The smallest of these units, ሳድሲት (sādsit), is just 1/540,000 of a second, or approximately 1.85 microseconds. The sequence can be extended still further—to ሳብኢት, ሥሙንቲት, ተሰዓቲት, and beyond—allowing mathematically ever smaller intervals of time to be expressed.

Time and the rhythms of life

These tiny units become easier to appreciate when compared with familiar natural rhythms.

  • A period of ፲፭ ራብዒት (0.1 second) is approximately the duration of the blink of an eye.
  • An አፍታ (afta), a brief interval associated with an adult, is given as ፲ ሣልሲት (4 seconds), roughly comparable to the interval between two blinks.
  • The duration associated with an adult heartbeat is approximately ፩ ተግማሽ to ፪ ተግማሽ ሣልሲት (0.6–1.0 second).

The same numerical system used to describe these fleeting moments can then be extended upward to measure days, months, years, and astronomical cycles.

The length of the year

The length of the solar year is:

፫፻፷፭ ዕለታት ከ፲፭ ኬክሮስ ፮ ካልዒት ፭ ሣልሲት
(365 days, 6 hours, 2 minutes, 2 seconds)

The Ethiopian calendar divides the ordinary year into ፲፪ months of ፴ days each. These twelve months account for 360 days. The remaining days form the short thirteenth month, ጳጉሜን (Pagumen).

Pagumen normally contains ፭ days. The additional ፲፭ ኬክሮስ (6 hours) in each solar year accumulates until, after ፬ years, it becomes one complete additional day. Pagumen consequently contains ፮ days in a leap year.

But the calculated year contains a small amount beyond those six hours: ፮ ካልዒት ፭ ሣልሲት (2 minutes, 2 seconds). If accumulated over a sufficiently long period, this residual fraction would produce another calendrical correction. Over ፮፻ years, it would amount to approximately another day, theoretically producing a Pagumen of seven days. Whether such a correction was historically incorporated into the Ethiopian calendar is uncertain.

The daily course of the Moon

The Moon’s daily course measured against the solar day is:

፶፱ ኬክሮስ ፫ ካልዒት ፵ ሣልሲት ፲፮ ራብዒት ፲፰ ሓምሲት ፵፰ ሳድሲት
(approximately 23 hours, 37 minutes, 28.11 seconds)

A complete solar day consists of ፷ ኬክሮስ (24 hours). The Moon’s daily course therefore falls short of a solar day by:

፶፮ ካልዒት ፲፱ ሣልሲት ፵፫ ራብዒት ፵፩ ሓምሲት ፲፪ ሳድሲት
(approximately 22 minutes, 31.89 seconds)

This shortfall is called ሕጸጽ, the deficiency or difference between the calculated period and the complete unit against which it is being measured.

Over ፲፭ days, the Moon’s course amounts to:

፲፬ ዕለት ፵፭ ኬክሮስ ፶፭ ካልዒት ፬ ሣልሲት ፬ ራብዒት ፵፪ ሓምሲት
(approximately 14 days, 18 hours, 22 minutes, 1.63 seconds)

The remaining amount needed to complete fifteen solar days is:

፲፬ ኬክሮስ ፬ ካልዒት ፭ ሣልሲት ፶፭ ራብዒት ፲፰ ሓምሲት
(approximately 5 hours, 37 minutes, 38.37 seconds)

The lunar month

A complete lunar month is:

፳፱ ዕለት ፴፩ ኬክሮስ ፶ ካልዒት ፰ ሣልሲት ፱ ራብዒት ፳፬ ሓምሲት
(approximately 29 days, 12 hours, 44 minutes, 3.26 seconds)

It therefore falls short of thirty complete days by:

፳፰ ኬክሮስ ፱ ካልዒት ፶፩ ሣልሲት ፶ ራብዒት ፴፮ ሓምሲት
(approximately 11 hours, 15 minutes, 56.74 seconds)

The traditional value for the lunar month is extraordinarily close to the modern mean synodic month. The difference is approximately:

፩ ሣልሲት ፱ ራብዒት ፲ ሳድሲት
(approximately 0.46 seconds)

In other words, the difference between the traditional value and the modern value is less than half a second over an entire lunar month.

The lunar year

Twelve lunar months produce a lunar year of:

፫፻፶፬ ዕለት ከ፳፪ ኬክሮስ ፩ ካልዒት ፴፯ ሣልሲት ፶፪ ራብዒት ፵፰ ሓምሲት
(354 days, 8 hours, 48 minutes, 39.15 seconds)

This is shorter than the solar year by:

፲ ዕለት ከ፴፯ ኬክሮስ ፶፰ ካልዒት ፳፪ ሣልሲት ፯ ራብዒት ፲፪ ሓምሲት
(10 days, 15 hours, 11 minutes, 20.85 seconds)

This difference explains one of the fundamental problems of lunisolar calendars. Twelve lunar months do not make a complete solar year, while thirteen lunar months exceed it. A larger cycle is therefore needed to bring the movements of the Sun and Moon back into close alignment.

(The text Alexandria is not correct. The coordinate (latitude, longitude) values are for the Adis Ababa observatory. The figure shows the Zodiac and the position of the planets as seen by an observer situated at the Adis Ababa observatory from 11-13. 09 .2026 of the Gregorian calendar.

ዐውደ አበቅቴ — the nineteen-year cycle

After ፪፻፴፭ lunar months, the phases of the Moon return to approximately the same position within the solar calendar. These ፪፻፴፭ months consist of ፻፳፭ long months of ፴ days and ፻፲ short months of ፳፱ days.

Their duration is approximately:

፷፱፻፴፱ ዕለታት ከ፵፩ ኬክሮስ ፳፪ ካልዒት ፶፯ ሣልሲት ፶፱ ራብዒት
(approximately 6,939 days, 16 hours, 33 minutes, 11.19 seconds).

A more precise value given for the same 235-month lunar cycle is:

፷፱፻፴፱ ዕለታት ከ፵፩ ኬክሮስ ፲፯ ካልዒት ፵፰ ሣልሲት
(6,939 days, 16 hours, 31 minutes, 7.2 seconds).

These ፪፻፴፭ lunar months correspond remarkably closely to ፲፱ solar years. Since a solar year is longer than twelve lunar months but shorter than thirteen, the nineteen-year period contains ፲፪ years of twelve lunar months and ፯ years of thirteen lunar months, giving a total of 235 months.

Ethiopian scholars call this cycle ዐውደ አበቅቴ (Awde Abəqte), also known as the Minor Computus. The Abəqte therefore completes one full cycle every ፲፱ years.

In Western astronomical tradition, the corresponding nineteen-year period is known as the Metonic cycle, named after Meton of Athens. Meton approximated its duration as ፷፱፻፵ days. The Babylonians were already using the nineteen-year cycle from approximately ፮፻ BC. In the Babylonian and Hebrew arrangement, the additional lunar month occurs in the ፫rd, ፮th, ፰th, ፲፩th, ፲፬th, ፲፯th, and ፲፱th years of the cycle.

For comparison, ፲፱ tropical years amount to:

፷፱፻፴፱ ዕለታት ከ፴፮ ኬክሮስ ፯ ካልዒት ፲፫ ሣልሲት
(6,939 days, 14 hours, 26 minutes, 53.2 seconds).

Compared with the more precise lunar value above, the difference is:

፲ ኬክሮስ ፲ ካልዒት ፴፮ ሣልሲት
(4 hours, 4 minutes, 14.4 seconds).

Using the Abushakir value for the solar year, however, the difference between ፪፻፴፭ lunar months and ፲፱ solar years is only:

፮ ኬክሮስ ፴፬ ካልዒት ፴፰ ሣልሲት ፲፩ ራብዒት
(approximately 2 hours, 37 minutes, 51.27 seconds).

The correspondence between 235 lunar months and nineteen solar years is therefore extremely close, though not exact. This small discrepancy (ሕጸጽ) gradually accumulates over longer periods.

Using the Abushakir values, twelve lunar months fall short of one solar year by:

፲ ዕለት ፶፫ ኬክሮስ ፬ ካልዒት ፳፯ ሣልሲት ፯ ራብዒት ፲፪ ሓምሲት
(approximately 10 days, 21 hours, 13 minutes, 46.85 seconds).

This annual difference explains the need for the seven additional lunar months distributed throughout each nineteen-year cycle.

Taking ፬ Awde Abəqte cycles together, and defining the solar year as:

፫፻፷፭ ዕለታት ከ፲፭ ኬክሮስ
(365 days and 6 hours),

the calculation reaches ፸፭ years, with a remainder of:

፫፻፷፭ ዕለታት ከ፳፰ ካልዒት ፵፯ ሣልሲት ፲፮ ራብዒት
(approximately 365 days, 11 minutes, 30.91 seconds).

From a heartbeat to nineteen years

Abushakir’s measurement system (or the more precisely the measurement system adopted by Abushakir) can describe both enormous astronomical cycles and extraordinarily small intervals of time.

The hierarchy begins:

ዕለት → ኬክሮስ → ካልዒት → ሣልሲት → ራብዒት → ሓምሲት → ሳድሲት

Each step divides the preceding unit by sixty. Beginning with the day and continuing through these successive divisions eventually produces ሳድሲት, a unit equivalent to approximately 1.85 microseconds.

Yet the same system also reaches in the opposite direction: from days to lunar months, from lunar months to years, and from years to the ፲፱-year ዐውደ አበቅቴ.

Time can therefore be followed continuously from fractions of a heartbeat to the recurring cycles of the Sun and Moon—all within the same mathematical framework.

For more details please refer: ጊዜ ፣ የኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር ቀመር እና የዘመናዊ ሥነፈለክ መንደርደሪያዎች | Zenodo










ዐድዋ

እንኳን ለ130ኛው የዐድዋ የድል በዓል አደረሰን። ዐድዋን ኢትዮጵያዊያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም መላው አፍሪካዊያን ፣ ወደ ፊት ደግሞ የሰው ልጆች ሁሉ (ሰው እኩለነቱን ይማርበታልና) ሊያከብሩት የሚገባ ጋናና እና አኩሪ ታሪክን የያዘ የነጻነት ተጋድሎ እና የድል በዓል ነው።

በልጅነቴ ካነበብኳቸው ፣ የአተራረካቸው ለዛ ከሚማርከኝ ከተክለ ጻድቅ መኩሪያ “ዐፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት” መጽሐፍ ውስጥ በወፍ በረር አሳጥሬ የያዝኩትን ከተለያዩ ምንጮች ከተገኙ የፎቶግራፍ መዝገቦች ጋር እነሆ…

ንጉሥ ምኒልክ ከቴዎድሮስ ካመለጡ በኋላ ፣ መጀመሪያ ወደ ወሎዋ ገዥ ወደሆነችው ወደ ወርቂቱ  በኋላም ወደ ትውልድ ሀገራቸው ወደ ሸዋ ሄደዋል። ንጉሥ ምኒልክ በዐፄ ቴዎድሮስ ተማርከው ሲሄዱ ሸዋን እንዲያስተዳደር በዐፄ ቴዎድሮስ የተሾመው በዛብህ ምኒልክን ወደ ሸዋ ላለማስገባት አንገራግሯል።

ንጉሥ ምኒልክ ወደ ሸዋ ከገቡ በኋላ ግዛታቸውን በማስፋፋት እና በማጠናከር ተጠምደዋል። በዐፄ ቴዎድሮስ ዘንድ በነበሩበት ጊዜ የፈረንጆቹን ብልኃት በመረዳታቸው ግንኙነት ለመፍጠር እና የእነሱን ብልኃት ወደ ሀገራቸው ለማስገባት ፍላጎት ነበራቸው። በተለይም የጦር መሣሪያ ለማስገባት ብዙ ጥረዋል። ከነዚህም ውስጥ ዋነኛው ከኢጣልያ መንግሥት ነው። ለዚሁም ከኢጣልያ መንግሥት ጋር ፔትሮ አንቶነሊ በተባለ የኢጣልያ መንግሥት ተወካይነት በ1880 የስምምነት ውል ተዋውለዋል። ውሉ የንጉሥ ምኒልክን እና የኢጣልያን መንግሥት የወዳጅነት ቃልኪዳን

  • የኢጣልያ መንግሥት ንጉሥ ምኒልክን በመሣርያም ሆነ በሌላ ጉልበታቸውን ለማጠንከር ርዳታ ያደርጋል ፣
  • ንጉሥ ምኒልክም በበኩላቸው የኢጣልያን መንግሥት ይረዳሉ ፣
  • የኢጣልያ መንግሥት የኢትዮጵያን መሬት የትም ቦታ እንዳይነኩ ፣
  • የኢጣልያ መንግሥት አሰብ ላይ ለሚገኝ የንጉሥ ምኒልክ ተወካይ 5ሺ ጠመንጃ ያስረክባሉ ፣
  • ንጉሥ ምኒልክም በበኩላቸው እኒህን ጠመንጆች የኢጣልያ ሰዎችን ለመውጋት እንዳያውሉ እውነተኛ ቃል ይሰጣሉ ይላል።

ዐፄ ዮሓንስ መተማ ላይ የወደቁበትን እና ከርሳቸው በኋላ የነበረውን በመኳንንቱ መካከል የነበረውን መሸካከር እና የሥልጣን ሽግግሩን ጊዜ እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀመው ጣሊያን የሀገሪቱን የቀይ ባሕር ጠረፍ ኤርትራ በሚል ስያሜ ይዟል። በዚህ ዘመን የነበረው የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስቴር የሲቺሊያው ፍራቸስኮ ክሪስፒ ነበር። ከዐፄ ዩሓንስ ኅልፈት በኋላ ጣሊያኖች የትግራይ መኳንንት ቆመው አይመክቱንም ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ስምምነት አለን ብለው አስበዋል። ምኒልክ ቢያንገራግሩም ደግሞ ሌሎች መኳንንትን እናስነሳባቸዋለን በሂደቱም ለኢጣልያ ሰፊ ግዛት እናገኛለን ብለው አስበዋል።

በዚህ ጊዜ ሁሉ ከዐፄ ምኒልክ ያልተለየው ኮንት አንቶነሊ የኢጣልያ መንግሥት የርሳቸው ወዳጅ እንደሆነ ፣ ጥቅማቸውን እንደሚጠብቅ ፣ የገንዘብ ብድርም ሆነ የጦር መሣሪያ ለማግኘት ግን በይፋ የስምምነት ውል ሲደረግ እና የኢትዮጵያ ዋና መልዕክተኛ ሮማ ሄዶ ከኢጣልያ ንጉሥ ጋር ሲገናኝ ነው በማለት ወትውቷቸዋል። በዚሁም ከሮማ የተላከለትን የውል ረቂቅ በግራዝማች ዮሴፍ (ፈረንሳይኛ የሚችሉ) ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንጉሡ ቀርቦ ምክር እና መለስተኛ ጥናት ከተደረገበት በኋላ በ20 አንቀጽ የተከፈለውን የውጫሌን ውል ተፈራራሙ። ነገር ግን የአማርኛው ትርጉም እና ጣሊያንኛው ልዩነት ነበራቸው። ከነዚህም ውስጥ የ17ኛ አንቅጽ ልዩነት ለዓድዋ ጦርነት ምክንያት ሆኗል።

የአንቅጽ 17 አማርኛው

“የኢትዮጵያ ንጉሠ ነግሥት ከአውሮፓ ነገሥታት ጋር ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣልያ መንግሥት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል።” ሲል የዚሁ አንቀጽ ጣሊያንኛው ደግሞ

“የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ ኃያላን ወይም መንግሥታት ጋር ለሚዋዋሉት ጉዳይ ሁሉ በግርማዊ የኢጣልያ ንጉሠ ነገሥት (አማካይነት) ለመጠቀም እሺ ብለዋል” የሚል ነው።

በ1885 እኤአ አፍሪካን ለመከፋፈል በበርሊን በተደረገው ስምምነት መሠረት ክሪስፒ ውሉን አባሪ አድርጎ ደብዳቤ በመላክ ውሉ በይፋ እንዲታወቅለት አድርጓል። ከተላከላቸው ሀገራት እንደ ፈረንሳይ ፣ እንደ መስኮብ እና ቱርክ ያሉት ሀገራት እንደ ኢትዮጵያ ነጻ ሆኖ የኖረ ሀገር የሌላውን ሀገር የበላይ ጠባቂነት በፈቃዱ እንዴት ይሰጣል በማለት በነገሩ ላይ ጥርጣሬ ስላደረባቸው ሁኔታውን ከአዲስ አበባ ለማጣራት ሲቆዩ ፣ ከጀርመን እና ከእንግሊዝ ግን እውቅና ተሰጥቶታል። ክሪስፒ ለዘለቄታ በኢትዮጵያ ላይ ጠባቂነትን ለኢጣልያ አስገኘሁ ብሎ በኢጣልያ ምክር ቤት ውስጥ ፎክሯል።

ዳግማዊ ምኒልክም በበኩላቸው የንግሥና ሥርዓታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ፣ ለፈረንሳይ ፣ ለጀርመን እና ለእንግሊዝ ነገሥታት የዕወቁልኝ ደብዳቤ ልከዋል። ምላሹም በውጫሌ ከተዋዋሉት ውስጥ 17ኛውን አንቀጽ  መሠረት በኢጣልያ መንግሥት ንጉሠ ነገሥት መሆንዎ ካልተላለፈለን አንቀበልም የሚል ነበር። ከነዚህ ነገሥታት ውስጥ ከጀርመን መንግሥት የመጣው ምላሽ ዐፄ ምኒልክን እና እቴጌ ጣይቱን አስቆጥቷል።

የኢጣልያ መንግሥት ዐፄ ምኒልክን በውል አፍራሽነት ለመወንጀል ተነሳስቷል። ዐፄ ምኒልክ ነገሩን በትዕግስት እና በሠላም ለመቋጨት በመፈለጋቸው ለኢጣልያ መንግሥት ስለሁኔታው የሚገልጥ ደብዳቤ ጽፈዋል።

ከጣሊያኑ ንጉሥ ከኡምቤርቶ ቀዳማዊ ፣ ይኸን ያደረግነው በሌሎች ኃያላን መንግሥታት ፊት የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ እንዲቻለን ስለወዳጅነታችን ነው የሚል አንድምታ ያለው እና ለዚሁም አመቺ እንዲሆን 17ኛውን አንቀጽ ተቀበሉ የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።

እንዲሁም ቀደም ብሎ ኮንት አንቶነሊ ልዑክ ወደ ኢጣልያ እንዲልኩ ንጉሥ ነገሥቱን በወተወታቸው መሠረት ራስ መኮንን ከግራዝማች ዮሴፍ እና ከሌሎች መኳንንት ጋር ሄደው የደመቀ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር።  እጅግ ትላልቅ ጥይቶችን የሚተኩሱ መድፎችን እንዲጎበኙ ተደርገዋል። ያረፉበትም ቦታ እጅግ የቅንጦት ቦታ ነበር። መስተንግዶው እንጎድቹን ለማስደነቅም ለማስደንገጥም ታቅዶ የተደረገ ይመስላል። በዚሁ ወቅት በኢጣልያ ጋዜጦች ላይ ሲወጣ የነበረውን የውጫሌ ስምምነት በተለይም አንቀጽ 17ን ያነበበው እና በወቅቱ ለትምሕርት ኢጣልያ ይገኝ የነበረው የዘጌው አፈወርቅ ስለነገሩ ክፉነት ለራስ መኮንን አሳውቋል።

ንጉሠ ነገሥቱ አንቀጽ 17 እንዲነሣ ካሳወቁበት ጊዜ ጀመሮ ጣልያኖቹ በመሸንገልም በማስፈራራትም ውሉ እንዲጸና ሞክረዋል። በተጨማሪም በጋዜጦቻቸው ዳግማዊ ምኒልክ ውል የማያከብሩ ፣ አገሪቱ ሥርዓት የማታውቅ ፣ ሕዝቡ ገና ካረመኔነት ያልተላቀቀ ፣ ሽፍታ እና የበሪያ ንግድ የሚያዘወትር ነውና ልናሰለጥነው ይገባል የሚል ፕሮፖጋንዳ ይነዙ ነበር።

ስለቀደመው የማደናገር ሥራው በወደ ኢጣልያ ተጠርቶ ሥልጣን የተሰጠው ኮንት አንቶነሊ ዐፄ ምኒልክን እንዲያግባባ እና በጣሊያንኛ የተጻፈውን ውል እንዲያስጸድቅ ወደ አዲስ አበባ ተልኳል።

ዐፄ ምኒልክ

  • የውሉን 17ኛ ክፍል መሰረዝ
  • በአማርኛ የተጻፈውን መቀበል
  • በሁለቱም ቋንቋዎች የተጻፈውን እንዳለ መተው።

የሚሉ ሦስት ምርጫዎችን ሰጥተውታል።

ኮንት አንቶነሊ የጣሊያንኛው ለስምምነቱ ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባል ብሎ መሟገቱን ቀጥሏል። ከብዙ ክርክር በኋላ ወደ ኢጣልያው ንጉሥ ኡምቤርቶ አንደኛ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እና የኮንት አንቶነሊ ፊርማ ያለበት ደብዳቤ ጽፈው ለመላክ ይስማማሉ። በደብዳቤው አንቶነሊ የጣልያንኛው ቀርቶ የአማርኛው ይሁን ቢሉት ከንጉሤ እና ከጠቅላይ ሚንስቴሩ ሳላስፈቅድ አልችልም ስለማለቱ እና አሁን ግን 17ኛው አንቀጽ በፍጹም እንዲቀር መስማማታቸውን ጽፈዋል። ጽሑፉ ላይ የንጉሠ ነገሥቱ እና የኮንት አንቶነሊ ፊርማ ተቀምጧል።

አንቶነሊ በአማርኛ የተጻፈውን እና የፈረመበትን ከቤቱ ወስዶ ባስተርጓሚ ሲያስተረጉመው 17ኛ አንቀጽ እንዲሰረዝ መስማማቱን የሚገልጽ መሆኑን ተረዳ። በማግስቱ በንዴት ወደ ቤተመንግሥቱ ሄዶ 17ኛ አንቀጽ ይቅር አላልኩም ብሎ አመለከተ። ዐፄ ምኒልክም በግልጽ ባስተርጓሚ የተነጋገርንበትን ቢጸጽትህም አይለወጥም አሉት። በዚህ ጊዜ አንተ ነህ ይኸን ያደረኝኸው ብሎ ግራዝማች ዮሴፍን ተሳደበ። እቴጌ ጣይቱ “ቢያጠፋስ እኛ እንቀጣዋለን እንጅ አንተ ምን አግብቶህ ትሰድበዋለህ” ብለው ገሰጹት። ውጫሌ ላይ የተፈራረምነው የፈረንሳዩ ቃል ይታይ ሲል ፣ እኛ የምናውቀው የአማርኛውን ነው አሉት። በብስጭት ፣ ከእንግዲህ ወዳጅነት ቀርቷል  ጦርነት ብቻ ነው በማለት ተሰርዟል የሚል ቃል ያለበትን ደብዳቤ ከፊታቸው ቀዶ ጣለው። እቴጌ ጣይቱ ከት ብለው በመሣቅ ጦርነቱን የዛሬ ሣምንት አድርገው በዚህ የሚደነግጥልህ የለም ብለው በቁጣ መልሰውለታል።

ኮንት አንቶነሊ ከዚህ በኋላ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ አውቋል። ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ተመካክረው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ወስነዋል። ይኸንኑ ውሳኔያቸውን ለዐፄ ምኒልክ በደብዳቤ አሳውቀዋል። ዐፄ ምኒልክም ያደረገው ድርጊት እንዳሳዘናቸው ፣ ለመሄድ ከቆረጡ እንደማይከለክሏቸው በጽሑፍ ገልጸውላቸዋል።  እነ ኮንት አንቶነሊ ለመሄድ ውሳኔ ላይ በመድረሳቸው ነጉሠ ነገሥቱ ለጉዞ የሚያስፈልገውን ሰጥተው ወደ ሀገሩ ልከውታል።

ጣሊያኖች እንደ ሌሎቹ የአውሮፓ ኃያላን ቅኝ ቅዛት ለማግኘት የቋመጡ በመሆናቸውን የዐፄ ምኒልክን የሰላም መንገድ ከምንም አልቆጠሩትም ነበር። ይልቁንም ራስ መንገሻ እና ራስ አሉላ ፣ ሌሎችም መሣፍንት በዐፄ ምኒልክ ላይ እንዲነሱ ለማድረግ ጥረት ማድረጉን ተያያዙት። ከራስ መንገሻ ጋርም የተወሰነ ስምምነት አደረጉ። የጣሊያኖቹ እንቅስቃሴ ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ለዐፄ ምኒልክ ታይቷቸዋል። አንቶነሊን ተክቶ ለመጣው የኢጣሊያ ተወካይ ወዳጃቸው የሆኑት ንጉሥ ኡምቤርቶ ይኸንን እንደማያደርጉ ምናልባት በምፅዋ የሚገኙ የበታች ሹማምንት አድርገውት ሊሆን እንደሚችል ይነግሩታል። ተወካዩ ከራስ መንገሻ ጋር ከተካሄደው ስምምነት ይልቅ ዐፄ ምኒልክን ወዳጅ መስሎ መያዝ አንቀጽ 17ን እንዲጸድቅ ማድረግ እንደሚቻል አስቧል። ይኸንኑ ሐሳቡን በኢጣሊያ የበላይ ሹማምንት ተቀባይነት እንዲያገኝ አድርጓል። በሂደቱም ጣሊያኖቹ ከራስ መንገሻ ጋር የገቡትን ስምምነት ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አሰብ ላይ ይዘውት የነበረውን ዐፄ ምኒልክ የገዙትን 2 ሚሊዮን ጥይት ለዐፄ ምኒልክ ለቀውላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከፈረንሳይ አዝዘው ሲጠባበቁ የነበረው 30 መድፍ ደርሶላቸዋል። በጣሊያኖች ክህደት የደረሰባቸው ራስ መንገሻ ጣሊያኖቹ ላይ አቂመዋል ፣ ከዐፄ ምኒልክ ጋር ታርቀዋል። ከዚህ በኋላ ዐፄ ምኒልክ በይፋ አንቀጽ 17 እንዲሰረዝ መጠየቅ ጀምረዋል።

ኢጣልያኖቹ አንቀጽ 17ን በማታለልም በማስፈራራትም ማጸደቅ አለመቻላቸውን ሲያዩ ፣ ለሌላ መንግሥት የጠባቂነት ስምምነት እንደማይሰጡ ቃል ይግቡልን እና ይሰረዝ ወደሚል ሐሳብ ሄደዋል። እቴጌ ጣይቱ ይኸ የኛ ጉዳይ እንጅ የኢጣልያ ምንግሥትን የሚያገባው አይደለም የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል ፣ ንጉሡም ይኸንኑ የእቴጌ ጣይቱን ሐሳብ አጽድቀዋል።

ኢጣሊያን ወክለው ሐሳብ ሲያመላልሱ የነበሩት እነ ትራቬሲ በጻፉት መጽሐፋቸው በገጸበረከት እና በሽንገላ እናታልላለን ብለው ራሳቸው መታለላቸውን ፣ በዲፕሎማሲ መበለጣቸውን ፣ ምኒልክ ጥሩ ዲፕሎማት መሆናቸውን ጽፈዋል።

ራስ መንገሻም በተለያየ ምክንያት ሸፍተው ወደ ጣሊያኖቹ ገብተው የነበሩ የጦር መኮንኖችን ውስጥ ለውስጥ በመላላክ ከጣሊያኖች ጉያ ለማውጣት ጥረት አድርገዋል። በብዙ ተሳክቶላቸዋል። በተለይም ጣሊያኖቹን በሀገር ተወላጅ ላይ የሚያደርሱትን ግፍ እና ንቀት የተመለከቱት እና ቁጭት ያደረባቸው ወደ ወገናቸው ለመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት አድሮባቸዋል።

ጣሊያኖችም ብዙ የኢትዮጵያ መኳንንትን ለማስከዳት እና እና በዐፄ ምኒልክ ላይ ለማሳመጽ ጥረት አድርገዋል ፣ ብዙ የሀገር ተወላጆችን በሰላይነት መልምለው አሰማርተዋል። 

ጣሊያኖች ሐማሴንን እና አከለ ጉዛይን እያለፉ እስከ መረብ ድረስ ተጠግተዋል። እንደውም ውጊያ ብንገጥም ብዙ መኳንንት ይተባበሩናል ብለው አስበዋል። ይኸን የጣሊያኖቹን መስፋፋት የተመለከቱት ራስ መንገሻ ጦራቸውን ይዘው ከዓድዋ ወደ መረብ ተጉዘው አከለ ጉዛይ አውራጃ ገብተዋል። ጣሊያኖቹ ይኸንን እንዳወቁ ለጦርነት ተሰልፈዋል። በራስ መንገሻ እና በጣሊያኖች መካከል ኮአቲት ላይ ጦርነት ተካሂዷል። ራስ መንገሻ በቂ የስንቅ ዝግጅት አልነበራቸውምና ወደ ሰናእፈ ተመልሰው መስፈር ነበረባቸው ይባላል። ይኸም የኢጣልያን ጦር ሞራል ከፍ በማድረጉ ተከታትለው ራስ መንገሻን ለመውጋት ወስነዋል። ሊመሻሽ አካባቢ ሰናእፈ ደርሰው በራስ መንገሻ ላይ ጦርነት ከፍተዋል። የራስ መንገሻ ጦር ዝግጅቱ ስላልነበረው ቦታውን ለቆ ተበታትኗል። ይኸን ዜና ጣሊያኖቹ ለሮማ ሹማምንት እያጋነኑ ቴለግራም አድርገዋል። ከዚህ በኋላ የኢጣልያን ጦር የሚያቆመው የለም ብለው አምነዋል። የባራቲየሪ ዝና በኢጣልያ ገኗል።

በጄኔራል ባራቲየሪ እና በምክትሉ በጄኔራል አሪሞንዲ የሚመራው የኢጣልያ ጦር ወደ ዓድዋ ፣ ወደ መቀሌ እና ወደ አዲግራት ተንቀሳቅሰው በየከተማው የምሽግ ዝግጅት እና ሹም ሽር አድርገዋል። ጄኔራል አሪሞንዲ ጊዜያዊ የትግራይ አስተዳዳሪ ሆኖ ተሾሟል።

ከዚህ ቀጥሎ ጣሊያኖች ደብረ ኃይላ መድረሳቸው ታውቋል። የራስ መንገሻ ሹማምንት መክረው ራስ መንገሻ ወደ ራስ ወሌ ግዛት እንዲሄዱ ተወስኗል። ወታደሮቻቸው ግን ደብረ ኃይላ ላይ ለመመከት ወስነዋል። በማዦር አሜሊዎ የሚመራው ብዙ ያገር ተወላጆችን የያዘ ጦር የደብረ ኃይላን መንደሮች ማቃጠል ሲጀምር ፣ ከሸዋ ወደ ራስ መንገሻ ከሄዱት ከነቀኝ አዝማች ኃይለማርያም ጦር ጋር ገጥሟል። ጣሊያኖቹ የተሻለ የጦር ዝግጅት እና ወታደራቸውም በቁጥር ብዙ ስለነበረ ጦርነቱን አሸንፈዋል።

ከዚህ በኋላ በደረሱበት ሁሉ ሹም ሽር እያደረጉ ከደብረ ኃይላ አልፈው አላጌን ከዚያም አልፈው አሸንጌ ሐይቅን ይዘዋል። ከዚህ በኋላ …የምኒልክን ባላንጦች ማበረታታት አለብን…የሚል መልዕክት ለባራቲየሪ  ደርሶታል። የኢጣሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ መሣፍንትን እና መኳንንትን በምኒልክ ላይ ለማስነሳት ጥረት አድርጓል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ፣ ዐፄ ምኒልክ ዲፕሎማሲያቸውን ሳያቋርጡ ለማይቀረው ጦርነት ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል። ጣሊያኖች ወደፊት ገፍተው አዲግራትን እና መቀሌን ይዘዋል። ከዚያም አልፎ ግንባር ቀደሙ የኢጣልያ ጦር ወደ አምባ አላጌ መገሥገሡን በዐፄ ምኒልክ ዘንድ ተሰምቷል። ምኒልክ በመስከረም ወር 1888 የሚከተለውን የክተት ዐዋጅ ዐውጀዋል

እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ ፣ አገር አስፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም። ደግሞም እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። እንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠራጠርም። አሁንም አገርን የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር። አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው! ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለምሽትህ፥ ለሃይማኖትህ፥ ለሀገርህ ስትል በሐዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጠላኛለህ ፣ አልተውህም! ማርያምን! ለዚህ አማላጅ የለኝም!  ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና እስከ ጥቅምት እኩሌታ የሸዋ ሰው ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ።

በራስ መኮንን አዝማችነት ግንባር ቀደም የሆነው ጦር ቀድሞ አላጌ ደርሷል። ራስ መንገሻም ጦራቸውን ይዘው ተቀላቅለዋል። በማዦር ቶዜሊ የሚመራው የኢጣልያ ጦር (ብዙ የሀገር ተወላጆች ያሉበት) አምባ አላጌ ላይ መሽጓል። ራስ መኮንን ነገሩን በሠላም ለመቋጨት ከጣልያን መኮንኖች ጋር ደብዳቤ ተጻጽፈዋል። ሂደቱ ግን ርባና ያለው ውጤት አላስገኘም ነበር። ራስ መኮንን ከቶዘሊ ጦር ጋር በታሕሳስ ሰባት 1888 ዓም ገጥመው የቶዜሊን ጦር ድል አድርገዋል። በጦርነቱም ማጆር ቶዘሊ ሕይውቱን አጥቷል። በጦርነቱ ላይ የራስ አሉላ እና የራስ መንገሻ ጦርም ተሳትፏል።

ከድሉ በኋላ አለ ትዕዛዝ ጦርነቱን የጀመሩት ፊታውራሪ ገበየሁ እና ቀኝ አዝማች ታፈሰ ታስረዋል። ለዐፄ ምኒልክም የድሉን ዜና በመልዕክተኛ አድርሰዋቸዋል። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በውጫሌ ፣ በባሻ ጨፌ ፣ በመርሳ እና በጭራ ወንዝ አድርገው በኦላ ወንዝ እና በጎሊማ አድርገው ሆርማት ላይ ሰፍረው ነበር።

የአምባ አላጌው ድል ኢጣልያኖቹን ወደ ቀልባቸው አልመለሳቸውም። ይልቁንም ተደፈርን በሚል ስሜት ለበቀል ተነሳስተዋል። አዳዲስ ጦርም ወደ ኤርትራ ማስገባት ጀምረዋል። በግዳጅም ፣ በኩርፊያም ፣ በድለላም ከኢጣልያኖች ጋር በተሰለፉት የሀገር ተወላጆች ዘንድ ግን ወደ እናት ሀገራቸው ለመመለስ መነሣሣትን ፈጥሯል። ብዙዎች ወደ ራስ መኮንን ጦር እየመጡ ተቀላቅለዋል።

ዐፄ ምኒልክ በመንገዳቸው እየመጣ የሚቀላቀላቸውን ጦረኛ እየተቀበሉ ከአዲስ አበባ በተነሱ በሦስተኛው ወር መጀመሪያ ላይ በታኅሣሥ 5 ወፍላ በ8 አሸንጌ በ 11 1888 ደምባልአ ላይ ደርሰዋል። ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከጎጃም ተነስተው በበጌምድር አድርገው ታኅሣሥ 15 ቀን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተገናኝተዋል። በ19 እንዳ መሆኔ በ23 ዋጀራት ገብተዋል። በ26 ጨለቆት ሰፍረዋል። ቀድመው የነበሩት ራስ ሚካኤል ፣ ራስ ወሌ ፣ ራስ መንገሻ ዩሓንስ፣ ራስ መንገሻ አቲከም ፣ ራስ መኮንን ፣ ራስ አሉላ እና ራስ ወልዴ ወደ ኋላቸው ተመልሰው ከነጉሠ ነገሥቱ ጋር ጨለቆት ላይ ተገናኝተዋል። በ28 ገናን አክብረው በ29 ከጨለቆት ተነስተው መቀሌ ሰፈሩ።

የጦሩ መሪሲያንስሲበዛ
ዳግማዊ ምኒልክ3400038000
እቴጌ ጣይቱ50006000
ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት50006000
ራስ ሚካኤል1400015000
ራስ መኮንን1500016000
ራስ ቢትወደድ መንገሻ50006000
ራስ ወሌ60007000
ራስ መንገሻ ዮሐንስ ፣ የራስ አሉላን እና የራስ ሐጎስን ጨምረው30004000
ፊታውራሪ ገበየሁ1300014000
ድምር110 000123 000

189000 ልዩ ልዩ ጠብመንጃ  ፣ ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ አራት ሺ ጥይት ፣ 46 መድፎች

በሰላይነት የተያዘው መሐንዲሱ ካፑቺ ወደ 68 500 ዝቅ ያደርገዋል። በአሁኑ ጊዜ ግን ቁጥሩን እየጨመሩ እስከ 200 000 አድርሰውታል።

ከአላጌው ጦርነት በኋላ የንጉሠ ነገሥቱን ጦር መቀሌ መስፈር ያወቀው ወደ ሹማምንቱ ጦር እና የጦር መሣሪያ እንዲላክለት ጠይቋል። የሚፈልገውን ሁሉ እንደሚልክለት ቃል የገባው ጠቅላይ ሚንስቲሩ ክሪስፒ አገሪቱ አንድ ሌላ ድል ከአንተ ትጠብቃለች ፣ ይኸም ድል የሐበሻን ጉዳይ ለዘለቄታው የሚደመድም መሆን አለበት። የራስህ እና የኢጣሊያ ክብር ያለበት ነው የሚል መልዕክት አስተላልፎለታል።

ራስ መኮንን ዛሬም የሰላም አማራጩን ላለመዝጋት በመቀሌ መሽጎ ለሚገኘው ለጋልያኖ ቦታውን ለቆ እንዲሄድ እስከ ምፅዋ የሚያደርሰው ሸኝ እንደሚሰጡት የሚገልጥ ደብዳቤ ለክውበታል። እርሱም እምቢታውን እና የትዕቢት መልሱን መልሷል።

ጣልያኖቹ ተኩስ በመጀመራቸው ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ባዘዙት መሰረት ሊቀመኳስ አባተ እና በጅሮንድ ባልቻ መድፍ እና መትረየሳቸውን ጠምደው ምሽጉን ይደበድቡት ጀመር።

ቢሆንም የኢጣሊያ ጦር ጥሩ ምሽግ መሽጎ ስለነበረ ብዙም ጉዳት አላደረሱበትም። በኋላ እቴጌ ጣይቱ ለጣሊያኖች አቅራቢያ የነበረውን እና ለመጠጥ ውኃ ይጠቀሙበት የነበረውን ምንጭ የራሳቸውን ወታደሮች አዘው አሲያዙት። ይህ ድርጊት የኢትዮጵያ ወታደሮችን ብዙ ሕይወት ሊያስከፍል ይችል የነበረውን የምሽግ መሥበር ውጊያ አስቀርቷል ፣ በውኃ ጥም ከሞት አፋፍ ላይ የደረሰው የኢጣሊያ ወታደር በትዕቢት ተወጥሮ የነበረው እና ቀድሞ ብዙ የደነፋው ማጆር ጋሊያኖ በውኃ ጥም ከማለቅ በንጉሡ መልካም ፈቃድ እና በራስ መኮንን ዋስነት ከምሽጉ ወጥቶ ወደ ወገኖቹ እንዲቀላቀል ሆኗል። ዐፄ ምኒልክም ለአንደኛው የኢጣልያ ሰው ከሀገራችሁ መምጣታችሁ የሰው ሀገር እንይዛለን ማለታችሁ ከጉድባ ውስጥ ገብቶ በውኃ ጥም ለማለቅ ነውን ፣ እኔ ግን የክርስቲያን ንጉሥ እንጅ የአሕዛብ ንጉሥ አይደለሁም… አሁንም ክርስቲያኖች በከንቱ አይለቁ ሰዎችህን ልከህ አስወስድ ትዋጉም እንደሆነ አንድነት ተሰብስባችሁ ጠብቁኝ እኔም እመጣለሁ ብለህ ለባራቲየሪ ንገረው አሉት።

ከዚህ በኋላ ጣሊያኖቹ ጦራቸውን እስከሚያደራጁ ፣ ምሽጋቸውን እስከሚያጠናክሩ ላይ ላዩን የእርቅ ወሬ ማውራት ጀምረዋል። ወደኋላ ላይ እብሪት የተሞላበት የመደራደሪያ ሐሳብ አቅርበዋል። የመደራደሪያ ሐሳቡ በአጭሩ ሲቀመጥ

  • የውጫሌ ውል ታድሶ እንዲረጋ ፣
  • የኢጣሊያ ባንዲራ እስከተሰቀለበት ያለው ሀገር የኢጣልያ እንዲሆን

የሚል ነው።

ዐፄ ምኒልክ ጦራቸውን ከመቀሌ አንስተው ወደ ሐውዜን ፣ ከሐውዜን ወደ ፈረስ ማይ ፣ ከፈረስ ማይ ወደ ሳውርያ ከዚያም ወደ ዐድዋ ታጥፈው የጦር ሰፈራቸውን የሐ የሚባለው ሥፍራ አድርገዋል።

በዚሁ ጊዜ ከራስ መንገሻ ጋር በነበራቸው ጠብ ለጣሊያኖች ገብተው የነበሩት ራስ ስብሐት እና ደጅ አዝማች ሐጎስ ተፈሪ ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ተቀላቅለዋል።

የኢትዮጵያ ሠራዊት ስንቅ የሚያጓጉዘው በባህላዊ መንገድ (ከዋናው የስንቅ መስፈሪያ ከቦሩ ሜዳ እና ከወረኢሉ ነው።) ወታደሩ ለብዙ ወራት በመንገድ በመቆየቱ ወታደሩ ሳይዋጋ ወይም ነገሩ በሠላም ሳይቋጭ ብዙ ለመቆየት የሚያስችለው ሀብት አልነበረም።

ጣልያኖቹ ምሽግ ሰርተዋል ፣ ከምሽጋቸው ምቾት ሆነው ጦርነቱን ሊያደርጉ ይፈልጋሉ። በተለይም የሀገር ተወላጆች ወደ ራሳቸው (ወደ ኢትዮጵያዊያን) ኃይል በመቀላቀላቸው ጦርነቱን ለመከላከል ሲቻል ለማዘግየት እንጅ  ከምሽግ ወጥተው ለመዋጋት መነሣሣቱ አልነበራቸውም። ኢትዮጵያዊያኑን በመተንኮስ ለውጊያ የተሰለፉ መስለው መልሰው ወደ ምሽጋቸው በመግባት ፣ ኢትዮጵያዊያኑ ምሽጉን ለመስበር እንዲዋጉ ለማነሣሣት እና ከምሽጉ ውስጥ ሆነው በመድፍ እና በመትረየስ ፈጅተው በቀላሉ ድል ለማድረግ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል።

ኢትዮጵያዊያኑም ጣልያኖቹ ከምሽጋቸው ወጥተው እንዲዋጉ ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ምግብ አልቆበት ለዘረፋ ተበትኗል ፣ እነራስ እከሌ እነ ራስ እከሌ ከድተዋል የሚል ወሬ ጣሊያኖች ሰላይ አድርገው በላኳቸው ሰዎች በኩል ማድረስ ጀምረዋል። አንዳንዶቹ መኳንንት ጦርነቱን ብትጀምሩ ወደ እናንተ እንገባለን ብለው እስከመጻፍ ደርሰዋል። ይኸ ዘዴ ሰርቶ ጣሊያኖቹ ከምሽጋቸው ወጥተው ለመዋጋት ወስነዋል።

 መሪየወታደር እና የመድፍ ብዛት
የኢጣልያን ጦር በዋናነት የሚመራው ጄኔራል ባራቲየሪ5000 አካባቢ የሚሆኑ ወታደሮች
ጄኔራል ዳቦርሜዳ3800 ወታደር 18 መድፍ
ጄኔራል አሪሞንዲ2493 ወታደር 12 መድፍ
ጄኔራል አልቤርቶኒ4076 ወታደር 14 መድፍ
ጄኔራል ኤሌና4150 ወታደር 12 መድፍ

ከዚህ ድል በኋላ በጄኔራል አልቤርቶኒ የዤኒራል አሪሞንዲ እና የዤኒራል ዳቦር ሜዳ ጦር ተሰልፎ ወጥቷል። ግንባር ቀደም ሆኖ የጀመረው በማዦር ቶሪ የሚመራው ጦር ነበር። ኢትዮጵያዊያኑ ስላየሉ ወደ ኋላው ሸሽቶ የአልቤርቶኒ የጦር ሰፈር ደርሷል። የኢትዮጵያዊያኑ ጦር እየተከታተለ ደርሶ ዋናው ጦርነት ተጀመሯል። የጀኔራል አልቤርቶኒ ጦር በመድፍ እና በመትረየስ አጥብቆ ተከላክሏል። የወታደሩን ማመንታት የተመለከተው ፊታውራሪ ገበየሁ የአምባላጌው አሸናፊ ፊት አውራሪ ገበየሁ በምን አኳኋን እንደሞተ ወደ ሸዋ በሕይወት የሚመለሱት ይናገሩ ብሎ ተናግሮ እንደ አንበሳ ተወርውሮ ወደ ጣሊያኖች መስመር ገብቶ 3 ሰዓት ላይ በመትረየስ ተመትቶ ኪዳነ ምሕረት እበሩ ላይ ወድቋል።

ንጉሡ ቀይ ዣንጥላቸውን አስዘርግተው ወደ ግንባሩ ዘልቀዋል። በአልቤርቶኒ የሚመራው የኢጣሊያ ጦር ሽሽት ጀምሯል። አልቤርቶኒ በፈረስ ሊሸሽ ሲል ፈረሱ ተመትቶ ወድቋል። ኢትዮጵያዊያኑ ደርሰው ማርከውታል። በዚሁ ጦርነት ራስ መኮንን እጃቸውን ቆስለዋል። ቁስላቸውን አስረው ውጊያውን ቀጥለዋል።

በጀኔራል አሪሞንዲ ጦር ፊትለፊት ለውጊያ የተሰለፉት ራስ ሚካኤል እና ራስ ወሌ ነበሩ። የጀኔራል አልቤርቶኒን ጦር የደመሰሰው የኢትዮጵያ ጦር በመካከል ሆነው ለሚዋጉት ለነራስ ወሌ ተደራቢ ሆኖ የአሪሞንዲን ጦር ገጥሞታል። ጄኔራል አሪሞንዲ እና ኮሎኔል ጋሊያኖ በዚሁ ጦርነት ላይ ሞተዋል።

ከዚህ ቀጥሎ ከሌሎቹ ተገንጥሎ በማርያም ሸዊት የነበረውን የዳቦርሜዳን ጦር ኢትዮጵያዊያኑ ደርሰው ከበው ገጥመውታል። ደቦርሜዳ እና ብዙዎቹ ተከታዮቹ በጦርነቱ ላይ አልቀዋል።

በወቅቱ የዐይን እማኝ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ጸሐፊ እንደገለጡት…

የካቲት 23 ቀን ከሌሊቱ 11 ሰዓት አካባቢ የኢጣሊያ ጦር በድንገት ደረሰ። ጦርነቱ ተጀመረ። የኢትዮጵያ ወታደር ወንድሙ ሲወድቅ ወንድሙ እያነሳው ፣ ጥይቱ ያለቀበት ከቆሰለው ወገብ ላይ እየወሰደ ተኩሱን ይቀጥላል። እቴጌ ጣይቱ ጥቁር ጥላ አስይዘው ዐይነ ርግባቸውን ገልጠው ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ልጅ በወይዘሮ ዘውዲቱ እና በደንገ ጡሮች ታጅበው ድሉ የኛ ነውና በለው እያሉ እንደ ወንድ ወታደሮቻቸውን አሰልፈው ወደ ጦርነቱ ገቡ።

የኢትዮጵያ ጦር ከጦርነቱ የሸሸውን የኢጣልያ ጦር እየተከታተለ ፣ የራቀውን በጥይት የቀረበውን በጦርና በጎራዴ እየመታ ፈጀው። ዐፄ ምኒልክ ወደፊት እየገፉ ጦር ያነሰበትን እየመረመሩ በፍጥነት እየላኩ ሲያዋጉ ዋሉ። የመጀመሪያው ድል የተፈጸመበት ቦታ እቴጌ መጥተው በእርኮት እና በገንቦ ያለውን ውኃ እና መጠጥ በገረዶች እያስቀዱ ቁስለኞቹን ኢትዮጵያዊያን እና ጣሊያኖቹም ሳይቀሩ እንዲጠጡ እና እንዲረኩ አደረጉ።

9 ሰዓት አካባቢ ያፄ ምኒልክ ጦር ምርኮ እየያዘ ሲመለስ ንግሥቲቱ ፣ ንጉሡ ሳይመለሱ ወዴት ነው የምትመለሰው ምርኮኛችሁን እየሰጣችሁኝ ወደዚያው ተመለሱ ብለው ጮሁባቸው። ዐፄ ምኒልክ ወደ ሠፈር ሲመለሱ ጊዜው መሽቶ ነበር።

ጳጳሱ አቡነ ማቲወስ እና የቀሩትም መነኮሳት የሚያጣጥረውን በማናዘዝ ፣ የሚሸሸውን እንዲመለስ በመገዘት የመንፈስ አባትነት ሥራቸውን ተወጥተዋል።

  • ከዐድዋ ድል ማግስት ምኒልክ የአውሮጫዊያንን ቀልብ ስበዋል
  • የሎንዶን ታይምስ ድሉ እስካሁን በንቀት ሲታዩ የነበሩ የአፍሪካውያንን መንፈስ ያነቃቃል የምኒልክ ድል የመላው አፍሪካዊያን ድል ነው ሲል ጽፏል።
  • የፓሪስ ዊክሊ ጋዜጣ የምኒልክን እና የጣይቱን ፎቶዎች በገጹ አትሟል።
  • የኒውዮርክ ታይምስ ሐበሾች ኢጣልያን አሸንፈዋል የሚል ኅትመት አውጥቷዋል።
  • የጦርነቱ ውጤት በኢጣልያ ሕዝብ ላይ የመሸበር እና የብስጭት ስሜት ጭሯል።
  • በመንግሥቱ ላይ አምጿል ፣ ቪቫ ምኒልክ ብሏል ፣ የክሪስፒ ሥርዓተ መንግሥት በመጋቢት 5 1896 ፈርሷል።
  • የእንግሊዝ የቅኝ ግዛት እና የውጭ ጉዳይ ቢሮዎች ምኒልክ በሶማሌ እና በሱዳን ያሉ የእንግሊዝን ንብረት ሊያጠቃ ይችላል ብለው ፈርተዋል።
  • በጥቅምት 23 1896 የኢትዮ ኢጣሊያን ጦርነት መጠናቀቅ በደንብ የሚያበስር ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈርሟል።
  • የውጫሌ ውል ተሰርዞ ኢጣልያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ተቀብላለች።
  • ኢጣልያ ፓርላማቸው ከወሰነ ኤርትራን ለኢትዮጵያ ለመመለስ ተቀብላልች።
  • በግንቦት 22 1897 የኢጣልያ ባለሥልጣናት በ222 ተቃውሞ እና በ140 ተቀብሎ የኤርትራን መመለስ ውድቅ አድርገዋል።
  • ኢጣልያ ላደረገችው የወረራ ጦርነት አፄ ምኒልክ 12 ሚሊዮን ሊሬ ካሳ ጥይቀዋል።
  • በግ ንቦት 14 897 እንግሊዝ የኢትዮጵያን ሉ አላዊነት ተቀብላለች።
  • እንዲሁም የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ከነበረችው የሶማሊያ ግዛት ጋር የነበረውን የድንበር ውዝግ እልባት ሰጥተዋል።
  • የኢትዮጵያ የግዛት ድንበሮች በ1897 ከእንግሊዝ እና ከፈረንሳይ ጋር በ1900 ከኢጣልያ ጋር በ1904 ከ ሱዳን የእንግሊዝ/ግብጽ አስተዳደር ጋር ፣ በ1908 ከእንግሊዝ ኬን ያ አስተዳዳሪዎች ጋር በተደረጉ ስምምነቶች የተጠበቁ ሆነዋል።
  • በቅኝ ግዛት ጭቆና ለነበሩ የአፍሪካ ሕዝቦች
    • የትምክህት ፣ የተስፋ ፣ የመነሳሳት ምክንያት እና የነጻነት ምሳሌ ሆኖላቸዋል
    • ዘረኝነትን ለመቀልበስ የእኩልነት ምሳሌ ሆኗል ፣ ከቅኝ ግዛት ቀንበር ለመውጣት በሚደረገው የምከታ ትግል ውስጥ ምልክት ሆኗል
  • ለአፍሪካ የነጻነት ሐሳብ መነሻ ሆኗል
    • አዲስ አበባን በ1904 የጎበኘ ቤኒቶ ሲልቫኒ የተባለ ሰው የፓናፍሪካዊነትን ሐሳብ አቀንቅኗል
    • ቀይ ፣ ቢጫ ፣ አረንጓዴ ቀለማት የፓናፍሪካዊነት ቀለማት ሆነው ተመርጠዋል
    • ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሰንደቅ ዓላማቸው ከቀይ ፣ ቢጫ ፣ አረንጓዴ ቀለማት ቀምረዋል።

የዐድዋ ጀግኖች የነጻነት መንፈስ ይደርብን ፣ አሜን

A brief recount of the Ethiopian history and the victory of Adowa – presented to the Ethiopian community in Trondheim during the celebration of the 128th and 129th Adowa victory

The following slides were presented at the celebration of the 128th Adowa Victory. The slides introduce the history of Ethiopia from ancient times to modern times. The slides recount the circumstances that led to the Adowa battle. They highlight the victory of the gallant Ethiopian forces at the battle.

የኢትዮጵያዊያን የዘመን አቆጣጠር

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን። በሚከተለው የፓወር ፖይንት ሰነድ ፣ እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጣር በ2016 ያቀረብኩትን ይዘት አካፍላለሁ።

የዔዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፍ (ግእዙ)

This note is concerned with the translation of the Geez part of Ezana’s stone transcription. The Ezana stone is a stone tablet that was transcribed during the time of Ezana commemorating Ezana’s military expeditions, victories and conquests. The transcriptions are in three languages; namely Geez, Sabean and Greek like the Rosetta stone.

https://zenodo.org/records/10069806

ኢትዮጵያውያን በሄሮዶቱስ የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ

በሄሮዱቱስ የታሪክ መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ከዋነኛ የታሪክ ተዋናዮች ውስጥ ናቸው። የሚከተሉት አንቀጾች ከሄሮዱቱስ የታሪክ መጽሐፍ የተተረጎሙ ኢትዮፕያውያንን የሚመለከቱ ትረካዎች ናቸው። ሄሮዶቱስ ከ፬፻፹፬ ቅልክ – ፬፻፳፭ ቅልክ የነበረ ፣ በወቅቱ ባካባቢው የነበረውን ታሪክ እና ትርክት ሰንዶ ያለፈ የጽርእ ሰው ነበር።

Files

Introduce Yourself (Example Post)

This is an example post, originally published as part of Blogging University. Enroll in one of our ten programs, and start your blog right.

You’re going to publish a post today. Don’t worry about how your blog looks. Don’t worry if you haven’t given it a name yet, or you’re feeling overwhelmed. Just click the “New Post” button, and tell us why you’re here.

Why do this?

  • Because it gives new readers context. What are you about? Why should they read your blog?
  • Because it will help you focus you own ideas about your blog and what you’d like to do with it.

The post can be short or long, a personal intro to your life or a bloggy mission statement, a manifesto for the future or a simple outline of your the types of things you hope to publish.

To help you get started, here are a few questions:

  • Why are you blogging publicly, rather than keeping a personal journal?
  • What topics do you think you’ll write about?
  • Who would you love to connect with via your blog?
  • If you blog successfully throughout the next year, what would you hope to have accomplished?

You’re not locked into any of this; one of the wonderful things about blogs is how they constantly evolve as we learn, grow, and interact with one another — but it’s good to know where and why you started, and articulating your goals may just give you a few other post ideas.

Can’t think how to get started? Just write the first thing that pops into your head. Anne Lamott, author of a book on writing we love, says that you need to give yourself permission to write a “crappy first draft”. Anne makes a great point — just start writing, and worry about editing it later.

When you’re ready to publish, give your post three to five tags that describe your blog’s focus — writing, photography, fiction, parenting, food, cars, movies, sports, whatever. These tags will help others who care about your topics find you in the Reader. Make sure one of the tags is “zerotohero,” so other new bloggers can find you, too.