Hulqu_V0

A few years ago, while studying Abushaker, I developed an algorithm to convert Arabic numerals into Geʿez numerals. I originally implemented the algorithm in Visual Basic and released it as an Excel add-in. I have since rewritten the code in Python (thanks to AI) and added a graphical interface.

This tool may be useful for researchers working with historical Geʿez documents, as well as for anyone interested in learning or studying the Geʿez numeral system. I am therefore releasing version 0 (V0) of the application here.

የቅምሮች እና የቀስቶ ሥፍሮች ሥነ-ስሌት

እንሆ…

በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት የቅምሮች እና የቀስቶ ሥፍሮች ሥነስሌት ነው። መጽሓፉ ስምንት ምዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ የሥነቅምርን ብያኔ ፣ ዐይነቶች እና ካርተሳዊ የቅንብር ሥርዓትን ይመለከታል። በሁለተኛው ምዕራፍ የቀስቶ ሥፍሮችን ብያኔ እና ሥነስሌት ይመለከታል። በሦስተኛው ምዕራፍ የዐሪካት ሥነስሌትን ይመለከታል። በዐራተኛው ምዕራፍ ለብዙ ሥሌቶች ጠቃሚ የሆኑ እና ዐሪካትን በምጥን ሒሳባዊ ሐረግ ለማስቀመጥ ምቹ የሆነው የመወስቅ ሥነስሌት ባጭሩ ቀርቧል። ምዕራፍ አምስት በከርቦች የተለያዩ ነጥቦች ላይ የሚሆኑ ተዳፋትን ፣ ተቃናትን ፣ ቅርበትን (ጥጌትን) ፣ ተቃረብን ፣ ከፊል እና ሙሉ ልውጠትን ለማስላት የሚጠቅሙ የስሌት ዘዴዎችን ይመለከታል። ምዕራፍ ስድስት የሬይማንን ድምር ፣ ሥነአልዶትን እና የአልዶት መተንተኛ መንገዶችን ባጭሩ ያቀርባል። ምዕራፍ ሰባት የቀስቶ መስኮችን ልውጠት እና አልዶት አተናተን እና በዚሁም ውስጥ ጠቃሚ የሆኑትን የግሪንን እና የጋውስን አዋጆች ያቀርባል። በመጨረሻው ምዕራፍ የከፍታ ፣ የዝቅታ እና የምጣኔ ስሌትን ባጭሩ ያቀርባል።

https://a.co/d/aOVRqz1

ሥነ-ቁጥር ወ ሥነ-ሥፍራ ዘዩክሊድ

እንሆ…

በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት ቁጥሮችን እና ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራን ነው። መጽሓፉ ሦስት ምዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ ቁጥሮች እና መሠረታዊ ስሌቶች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሥነ-ንጽጽር ድንጋጌዎች በቁንጽል ቀርበዋል። በሦስተኛው ምዕራፍ ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራ መሠረታዊ ብይኖች ፣ ድንጋጌዎች፣ አዋጆችን ከነማረጋገጫቸው ቀርበዋል። ዘዌዎች ፣ ተመሳሳይነት ፣ የፓይታጎረስ አዋጅ ፣ ክፍላተ ቅንብባት ከብዙ አዋጆች እና ማረጋገጫ ጋር ተመርጠው ቀርበዋል። የሥነ-ሥፍራ ድርሰቱ የተመረጠው ከጥንታዊው የግሪክ የሥነ-ሥፍራ ሊቃውንት ድርሰቶች በመሆኑ በዘመናዊ (ትንተናዊ ፣ ካርተሳዊ) ሥነ-ሥፍራ የተቃኘ አንባቢ ከመሠረታዊ ድንጋጌዎች ጀምሮ እያንዳንዱን አዋጅ በርጋታ ማየት ይኖርበታል።

መልካም ንባብ!

Amazon.com: ሥነ-ቁጥር ወ ሥነ-ሥፍራ ዘዩክሊድ (Amharic Edition): 9788269358308: Tsegaye, Anteneh Biru: Books