እንሆ…
በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት ቁጥሮችን እና ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራን ነው። መጽሓፉ ሦስት ምዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ ቁጥሮች እና መሠረታዊ ስሌቶች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሥነ-ንጽጽር ድንጋጌዎች በቁንጽል ቀርበዋል። በሦስተኛው ምዕራፍ ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራ መሠረታዊ ብይኖች ፣ ድንጋጌዎች፣ አዋጆችን ከነማረጋገጫቸው ቀርበዋል። ዘዌዎች ፣ ተመሳሳይነት ፣ የፓይታጎረስ አዋጅ ፣ ክፍላተ ቅንብባት ከብዙ አዋጆች እና ማረጋገጫ ጋር ተመርጠው ቀርበዋል። የሥነ-ሥፍራ ድርሰቱ የተመረጠው ከጥንታዊው የግሪክ የሥነ-ሥፍራ ሊቃውንት ድርሰቶች በመሆኑ በዘመናዊ (ትንተናዊ ፣ ካርተሳዊ) ሥነ-ሥፍራ የተቃኘ አንባቢ ከመሠረታዊ ድንጋጌዎች ጀምሮ እያንዳንዱን አዋጅ በርጋታ ማየት ይኖርበታል።
መልካም ንባብ!
Amazon.com: ሥነ-ቁጥር ወ ሥነ-ሥፍራ ዘዩክሊድ (Amharic Edition): 9788269358308: Tsegaye, Anteneh Biru: Books
